ግሎባል ፈንድ ዘንድሮ የለም

የግሎባል ፈንድ 11ኛው ዙር እንዲቋረጥ ለጋሾቹ ወስነዋል፡፡

ኤድስን፣ ሣምባ ነቀርሣንና ወባን ለመዋጋት የተመሠረተው ግሎባል ፈንድ አሥረኛ ዓመቱን እነሆ አከበረ፡፡ በዚህ ዕድሜው ታዲያ የሕክምና የመከላከልና የእንክብካቤ መርኃግብሮችን በመደገፍ ከሰባት ተኩል ሚሊየን በላይ ህይወቶችን ከጥፋት ማትረፉን ግሎባል ፈንድ እራሱ አስታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ የዚህ ዓመቱን ልገሣውን ባለፈው ኅዳር ሠርዟል፡፡ እስከ 2014 ዓም (እአአ) አዲስ በጀት እንደማያፀድቅም ገልጿል፡፡

ለጋሾች ፈጥነው ሃሣባቸውን ካላስተካከሉ ሊከተል የሚችለውን አደጋ አንድ ዓለምአቀፍ ፀረ-ኤድስ ድርጅት እያስጠነቀቀ ነው፡፡

ግሎባል ፈንድ ሦስቱን ግዙፍ ገዳይ በሽታዎችና ወሰን ዘለል ወረርሽኞች ለመዋጋት በዓለም ዙሪያ እያዋለ ያለውን ገንዘብ ማሰባሰብ የጀመረው በአውሮፓ አቆጣጠር በ2002 ዓ.ም ወይም በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር በ1994 ዓ.ም ነበር፡፡

ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ ታዲያ በ150 ሃገሮች ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ መርኃግብሮችን ለማከናወን ከ22 ሚሊየን ዶላር በላይ አፅድቆ አከፋፍሏል፡፡

ለጋሾቹ ወደ ሃምሣ የሚሆኑ ሃገሮች ሲሆኑ ከያንዳንዱ ዓመት ልገሣ 33 ከመቶውን ድርሻ የምታዋጣው ዩናይትድ ስቴትስ ግዙፏ ሰጭ ሃገር ነች፡፡ አሜሪካ በ2010 ዓ.ም ብቻ ከአንድ ቢሊየን ዶላር በላይ ረድታለች፡፡

የግሎባል ፈንድ አመራር ቦርድ አባላት ኅዳር ውስጥ ጋና ዋና ከተማ አክራ ላይ ተሰብስበው መጭውን የልገሣ 11ኛ ዙር ለመሠረዝ ተስማምተው ተበትነዋል፡፡

ዓለምአቀፉ የኤችአይቪ/ኤድስ ጥምረት ታዲያ በግሎባል ፈንድ ላይ ሰሞኑን ካወጣው አዲስ ሪፖርት ጋር “DON’T STOP NOW!” [“አሁን አታቁሙት!”] የሚል ዘመቻ ከብርቱ ማስጠንቀቂያና የመፃዒ አደጋ ማሣያዎች ጋር አውጇል፡፡

ዝርዝሩን ያዳምጡ፡፡