ግሎባል ቮይስስ #FreeZone9Bloggers የትዊተር ዘመቻ አዘጋጀ

የታሠሩት ብሎገሮችና ጋዜጠኞች /የፎቶ ምንጭ - ኢንተርኔት/

ግሎባል ቮይስስ - Global Voices የአንድ ቀን #FreeZone9Bloggers (የዞን ዘጠኝ ብሎገሮችን ልቀቁ) ዓለምአቀፍ የትዊተር ዘመቻ ለረቡዕ፤ ግንቦት 6/2006 ዓ.ም ጠርቷል፡፡




ግሎባል ቮይስስ - Global Voices የአንድ ቀን #FreeZone9Bloggers (የዞን ዘጠኝ ብሎገሮችን ልቀቁ) ዓለምአቀፍ የትዊተር ዘመቻ ለረቡዕ፤ ግንቦት 6/2006 ዓ.ም ጠርቷል፡፡ የዘመቻው ዓላማ ኢትዮጵያ ውስጥ የታሠሩ ዘጠኝ ጋዜጠኞችና ብሎገሮች (የኢንተርኔት አምደኞች) ትኩረት እንዲያገኙ ማድረግ ነው፡፡ ስለአዘጋጆቹ ይበልጥ ማወቅ ከፈለጉ ትዊት ያድርጓቸው፡፡ ናይጀሪያዊያኑ ብሎሰም ኖዲም Blossom Nnodim (@blcompere) እና ንዋቹክዉ ኤግቡኒኬ Nwachukwu Egbunike (@feathersproject)፣ እንዲሁም ታንዛኒያዊው የግሎባል ቦይስስ ኤዲተር - ንዴሳንጆ ማቻ Ndesanjo Macha (@ndesanjo) ናቸው፡፡ ረቡዕ፣ ግንቦት 6/2006 ዓ.ም በምዕራብ አፍሪካና ለንደን ሰዓት አቆጣጠር ልክ ከቀትር በኋላ በስምንት ሰዓት (2:00P.M.)፤ በምሥራቅ አፍሪካና በአዲስ አበባ ሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት በኋላ በ11:00 ሰዓት (5:00P.M.)፤ በምሥራቅ ዩናይትድ ስቴትስና በዋሽንግተን ሰዓት አቆጣጠር ከረፋዱ በአራት ሰዓት (10:00A.M.)፤ በምዕራብ ዩናይትድ ስቴትስ - ፓሲፊክ አቆጣጠር ከጠዋቱ በ7፡00 ሰዓት፤ አውስትራሊያ - ሲድኒ፤ ረቡዕ ለሐሙስ አጥቢያ ዕኩለ-ሌሊት ላይ (Wednesday, 24:00) ያግኟቸው፡፡ ከማኅበረሰብ መሪዎች፣ ከዲፕሎማቶች፣ ዋና ዋና ከሚባሉ መገናኛ ብዙኃን ጋር ትዊት ይደራረጋሉ፤ የግንዛቤ ማስጨበጫ መረጃዎችን ይለዋወጣሉ፡፡