“ይህን እንዴት አድርጌ ነው፤ ለሴቶች ልጆቼ የማስረዳው?” ብለው የጨነቃቸው አሜሪካውያን እናቶችም ብዙዎች ናቸው።
ለመሆኑ በዚህ በሴቶች ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ለማስመዝገብ በተደረገው ሙከራ ላይ የደረሰው ምንድነው?
የምርጫው ዕለት ማክሰኞ ማታ ውጤቱን በከፍተኛ ጉጉት ዓይናቸውን ተክለው ይከታተላሉ፡፡
የሚጠብቁት ሂላሪ ክሊንተን አሸንፈው ሴቶች በፍጥረታቸው ከወንዶች ጋር እኩል መሆናቸውን የሚያረጋግጠውን ድል።
እናቶች ሴቶች ልጆቻቸውን ይህንኑ ሊያረጋግጡላቸው ወደ ድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ይዘዋቸው ሄደዋል።
አንዲት እናት እንዲህ አሉ
“ህይወትን የሚቀይር ታሪክ ነው። ሴቶች ልጆቼ … ሴት ልጅ ፕሬዚዳንት መሆን እንደምትችል ምንጊዜም ቢሆን የገነዘባሉ፤ ስለዚህም ማንም ይህን፣ ያንን ማድረግ አትችሉም ሊላቸው አይችልም።”
በደምብ ነዋ! ፕሬዚዳንት ለመሆን እንችላለን”
ሂላሪ ክሊንተንም በምርጫው መሸነፋቸውን በተቀበሉበት ንግግራቸው ሴቶች ልጆቻቸውን አበረታተዋል።
“ክብር የሚገባችሁ ጠንካሮች መሆናችሁን ከቶ እንዳትጠራጠሩ፣ በዓለም ያለውን ዕድል በሙሉ ተጠቅማችሁ ህልማችሁን በጥረታችሁ ዕውን ከማድረግ የሚከልክላችሁ ነገር መኖር እንደሌለበት እንዳትጠራጠሩ”
ለመሆኑ ምንድነው የተፈጠረውና እና ሂላሪ የተሸነፉት?
የቪኦኤዋ ካሮሊን ፐርሱቲ ከኒውዮርክ ያስተላለፈችውን ዘገባ ቆንጂት ታየ ታቀርባለች።
Your browser doesn’t support HTML5