ባለፈው ሳምንት ጋና ውስጥ በተካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ያሸነፉት ናና አኩፎ አዶ በሚቀጥለው ወር ቃለ መሃላ ፈፅመው መንበረ ሥልጣን ይረከባሉ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
አዲሱ ፕሬዚዳንት ህይወታቸውን ሙሉ በጋና ፖለቲካ ውስጥ ያሳለፉ ሲሆኑ ናና አኩፎ አዶ ለፕሬዚዳንትነት ያሸነፉት ምጣኔ ሃብቱን አስተከክላለሁ ብለው ቃል በመግባታቸው ነው።
ሀገሪቱ ነዳጅ ዘይት እያመረተች ቢሆንም ዕዳ አየተጫናት ሙስናው እያተባባሰ የሥራ አጡም ቁጥር እየጨመረ ተቸግራለች።
ፍራንቼስካ ካክራ ፎርሰን ከዋና ከተማዋ ከአክራ ቀጣዩን ዘገባ ልካለች፤ ቆንጅት ታየ ታቀርበዋለች፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5
አዲሱ የጋና ፕሬዚዳንት ናና አኩፎ አዶ በሚቀጠለው ወር ሥልጣን ይረከባሉ