የጀርመኗ ቻንስለር አንጌላ መርክል “የክርስቲያን ዲሞክራሲያዊ ህብረት” ፓርቲያቸውን ለ18 ዓመታት ከመሩ በኋላ ዛሬ ተነስተዋል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
የጀርመኗ ቻንስለር አንጌላ መርክል “የክርስቲያን ዲሞክራሲያዊ ህብረት” ፓርቲያቸውን ለ18 ዓመታት ከመሩ በኋላ ዛሬ ተነስተዋል።
መርክል /CDU/ ሐምቡርግ ባካሄደው ጉባዔ ላይ ባደረጉት የሥንብት ንግግር፣ የሥራ ባልደረቦቻችውንና ረዳቶቻቸውን አመስግነዋል። ፓርቲያቸው ባንድ ግለሰብ የተመራ ሳይሆን አባላቱ ሁሉ ባንድነት በአበረከቱት አስተዋፅዖ ሲንቀሳቀስ እንደቆየም አስረድተዋል።
አንጌላ መርክል 30 ደቂቃ በፈጀው በዚህ የሥንብት ንግግራቸው ወቅት ጉባዔተኛው በተደጋጋሚ ከመቀመጫው በመነሳት ሞቅ ያለን ረዘም ያለ ጭብጨባ አድርጎላቸዋል። አንዳንድ የምክር ቤት ተወካዮች “አለቃችንን እናመሰግናለን” የሚሉ የጽሁፍ መፈክሮችን አስነብበዋል።
የ64 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ቻንስለር መርክል፣ ሥልጣን የሚለቁት ባላቸው ሊበራል የፍልሰተኞች ፖሊሲ ምክንያት የነበራቸው የሕዝብ ድጋፍ እየቀነሰ በመምጣቱ ነው ተብሏል።