ግድቡ ውኃ መያዝ ጀምሯል

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ውኃ መያዝ መጀመሩን የሚያሳዩ የሳተላይት ምስሎች ወጥተዋል።

ስለ ሳተላይት ምስሎቹ ይዘት የተጠየቁት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የቀረበላቸውን ጭብጥ አላስተባበሉም፤ እንዲያውም “እንደዚያ መውሰድ ይቻላል” ብለዋል። በምስሎቹ ላይ ትንታኔ መስጠት ግን አስፈላጊ ነው ባለው እንደማያስቡ አክለው ገልፀዋል።

በአፍሪካ ኅብረት አስተባባሪነትና ታዛቢነት “ቀሪ” በተባሉ የቴክኒክና የሕግ ጉዳዮች ላይ እየተካሄደ ያለው የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የግብፅ ድርድር በመልካም ሁኔታ እየተካሄደ እንደሆነም አምባሳደር ዲና ተናግረዋል።

በሃገሮቹ መካከል መግባባትን ለመፍጠርና “የአፍሪካ ሃብት ጉዳይ በአፍሪካዊያን እንዲያልቅ” የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ወደ አፍሪካ ኅብረት መምራቱን ኢትዮጵያ እንደምትደግፈው አምባሳደር ዲና ጠቁመው መተማመንን ለመፍጠርና በግርጌ ሃገሮች ላይ ጉዳት ሳይደርስ ውኃው ለጋራ ልማት ሊውል የሚችልበት መግባባት ለመድረስ ይቻላል የሚል ተስፋ እንዳላቸውም ተናግረዋል።

ሦስቱ ሃገሮች ስምምነት ላይ ለመድረስ አስበው የጀመሩት ንግግር በታለመለት ጊዜ ያልቃል ብለው እንደሚያስቡም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ገልፀዋል።

ከአምባሳደር ዲና ሙፍቲ ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ግድቡ ውኃ መያዝ ጀምሯል