ጉባ አካባቢ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 15 ሰዎች መገደላቸው ተገለፀ

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

ጉባ አካባቢ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 15 ሰዎች መገደላቸው ተገለፀ

ባለፈው ሳምንት የኅዳሴ ግድብ ሠራተኞችን ጭኖ ወደ ግድቡ ሲጓዝ በነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስና በእጀባ ላይ በነበሩ የፀጥታ ኃሎች ላይ በታጣቂዎች ተፈፀመ በተባለ ጥቃት 15 ሰዎች መገደላቸውን ከጥቃቱ የተረፉ መሆናቸውን የተናገሩ ሰዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።

ጥቃቱ የደረሰው የካቲት 23/2014 ዓ/ም መሆኑንና ቦታውም ጉባ ወረዳ አይሲድ ንዑስ ቀበሌ አፍሪካ እርሻ ልማት ተብሎ በሚጠራው አከባቢ እንደሆነ ተናግረዋል።