ጆርጅ ኤች ዋከር ቡሽ እየተሸኙ ነው

  • ቪኦኤ ዜና
ፕሬዚዳንት ጆርጅ ኧርበርት ዋከር ቡሽ /ፎቶ ፋይል፤ ጥር 2010 ዓ.ም./

ፕሬዚዳንት ጆርጅ ኧርበርት ዋከር ቡሽ /ፎቶ ፋይል፤ ጥር 2010 ዓ.ም./

የዩናይትድ ስቴትስ አርባ አንደኛ ፕሬዚዳንት የነበሩት የጆርጅ ኧርበርት ዋከር ቡሽ አስከሬን ከዛሬ፣ ሰኞ ኅዳር 24/2018 ዓ.ም አንስቶ በተወካዮች ምክር ቤቱ አዳራሽ ውስጥ ለተሰናባች ክፍት ሆኖ እንደሚቀመጥ ተገልጿል።

የዩናይትድ ስቴትስ አርባ አንደኛ ፕሬዚዳንት የነበሩት የጆርጅ ኧርበርት ዋከር ቡሽ አስከሬን ከዛሬ፣ ሰኞ ኅዳር 24/2018 ዓ.ም አንስቶ በተወካዮች ምክር ቤቱ አዳራሽ ውስጥ ለተሰናባች ክፍት ሆኖ እንደሚቀመጥ ተገልጿል።

የፕሬዚዳንት ጆርጅ ኧርበርት ዋከር ቡሽን አስከሬን የያዘው ሣጥን አገልጋያቸው ከነበረችው ውሻቸው ሳሊ ጋር

የፕሬዚዳንት ጆርጅ ኧርበርት ዋከር ቡሽን አስከሬን የያዘው ሣጥን አገልጋያቸው ከነበረችው ውሻቸው ሳሊ ጋር

በዋሺንግተን ዲ.ሲ. ጊዜ ከዛሬ ተስያት አንስቶ እስከ ከነገ በስተያ ረቡዕ ረፋድ ድረስ በተወካዮች ምክር ቤቱ ዋና እልፍኝ በሚያርፈው አስከሬናቸው በሚገኝበት ሣጥን አጠገብ ባለሥልጣናቱና ማንም ክብሩን ለቸራቸው የሚሻ ሁሉ እያለፈ ይሰናበታቸዋል።

ከነገ በስተያ ረቡዕ በመላ ዩናይትድ ስቴትስ ብሄራዊ የኀዘን ቀን ሆኖ እንዲውል መንግሥቱ አውጇል፤ ፌደራል መሥራያ ቤቶች ሁሉም ዝግ ሆነው ይውላሉ። ያኔ አሜሪካ በዋሺንግተኑ ብሄራዊ ካቴድራድል በሚካሄድ ሥነ-ሥርዓት አርባ አንደኛውን ፕሬዚዳንቷን ትሸኛለች።

አስከሬናቸውን ጭና ዛሬ ወደ መናገሻዪቱ ዋሺንግተን ዲሲ የበረረችው ‘ኤር ፎርስ ዋን’ ፕሬዚዳንታዊ አይሮፕላን በማግሥቱ ሐሙስ ወደዚያው ወደ ቴክሳስ ይዛ ትመለስና ሥርዓተ-ቀብሩ በስማቸው በሚጠራው ቤተ-መፃሕፍታቸው ይፈፀማል።

ስለ ፕሬዚዳንት ቡሽ ሰሞኑን ብዙ መልካም መልካም ቃላት የተናገሩት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕና ቀዳሚቱ እመቤት ሜላኒያ ትረምፕ በከነገ በስተያው የብሄራዊ ካቴድራል ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደሚገኙ ተነግሯል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ጆርጅ ኤች ዋከር ቡሽ እየተሸኙ ነው