ዜና ዕረፍት

ወይዘሮ ገነት ዘውዴ

ወይዘሮ ገነት ዘውዴ

ባልደረባችን ሰሎሞን ክፍሌ ባለቤቱን አጥቷል፡፡
ወይዘሮ ገነት ዘውዴ

ወይዘሮ ገነት ዘውዴ

Your browser doesn’t support HTML5

ባልደረባችን ሰሎሞን ክፍሌ ባለቤቱን አጥቷል


የሰሎሞን ክፍሌ ባለቤት ወ/ሮ ገነት ዘውዴ ያረፈችው በጠና ታምማ ላለፉት ሦስት ወራት ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ጆርጅ ዋሽንግተን ሆስፒታል በሕክምና ስትረዳ ከቆየች በኋላ ነው፡፡

ወ/ሮ ገነት ያረፈችው በቅርብ ሲንከባከቧት በነበሩት ባለቤቷ፣ ልጅዋ እናቷ፣ አክስቷና ሌሎችም የቤተሰብ አባላትና የቤተሰቡ ወዳጆች በተገኙበት ነው፡፡

ወ/ሮ ገነት ዘውዴና አቶ ሰሎሞን ክፍሌ በረዥሙ የትዳር ዘመናቸው አንዲት ልጅ አፍርተዋል፡፡
ወይዘሮ ገነት ዘውዴ

ወይዘሮ ገነት ዘውዴ

የወ/ሮ ገነት ዘውዴ ቤተሰቦች አርሊንግተን ቨርጂንያ፤ ኮሎምቢያ ፓይክ ላይ በሚገኘው የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አዳራሽ ውስጥ ዘመድ ወዳጅን እያስተናገዱ ሲሆን የፊታችን ሐሙስ፤ አፕሪል 3/2006 ዓ.ም ዋሽንግተን ዲ.ሲ በምትገኘው ርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የፀሎት ሥነ-ሥርዓት ተከናውኖ አስከሬኑ ወደ ትውልድ ሃገሯ ኢትዮጵያ በዚያው የሚሸኝ መሆኑን የቤተሰቡ አባላት ገልፀዋል፡፡

የቪኦኤ ባልደረቦች በተወዳጅዋ ጓደኛችን ወ/ሮ ገነት ዘውዴ ዕረፍት በእጅጉ አዝነናል፤ ለመላ ቤተሰብና ወዳጅ ዘመድ መፅናናትን እንመኛለን፡፡