ኮቪድ-19 በት/ቤቶች ላይ የፈጠረው ጫና

  • ቪኦኤ ዜና
የተመድ ዋና ፀኃፊ አንቶንዮ ጉቴሬዥ

የተመድ ዋና ፀኃፊ አንቶንዮ ጉቴሬዥ

በዓለም ዙሪያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ በማስገደዱ ዓለማችን በህፃናትትምህርት ላይ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚዘልቅ የከበደ አደጋ ተደቅኖበታል ሲሉ የተመድ ዋና ፀኃፊ አንቶንዮ ጉቴሬዥ አሳሰቡ።

ዋና ፀኃፊው ይህን ያሳሰቡት "መፃኢ ተስፋችንን እንታደግ" በሚል ርዕስ የመንግሥታቱ ድርጅት የጀመረውን አዲስ ዘመቻ ትናንት ባስተዋወቁበት ንግግራቸው ነው።

የዘመቻው ዓላማ በድህረ ኮቪድ-19 መደበኛ ትምህርትን መመለስና ማጠናከር ላይ ትኩረት መስጠት መሆኑ ተገልጿል።

እኤአ ሃምሌ አጋማሽ ድረስ በ106 ሃገሮች ከ1ቢሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸውና 40ሺህ ህፃናት ደግሞ ከመዋዕለ ህጻናት ውጪ ሆነዋል ብለዋል።

ወረርሽኙን ከተቆጣጠርን በኋላ ቅድሚያ ትኩረታችን ህፃናትን ወደትምህርት ገበታቸው መመለስ መሆን ይኖርበታል ሲሉ አሳስበው በተለይም አካል ጉዳተኞች፣ ልጃገረዶች፣ ስደተኞችና ተፈናቃዮች የተለየ ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ አስገንዝበዋል።