የጌዴኦ ባህላዊ መልክአ ምድር እና የባሌ ተራሮች በዓለም ቅርስነት ተመዘገቡ

Your browser doesn’t support HTML5

የጌዴኦ ባህላዊ መልክአ ምድር እና የባሌ ተራሮች በዓለም ቅርስነት ተመዘገቡ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኘው የጌዴኦ ባህላዊ መልክአ ምድር እና በኦሮሚያ ክልል የሚገኙት የባሌ ተራሮች፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (UNESCO) የዓለም ቅርስ ሆነው ተመዘገቡ።

መልክአ ምድሩ በቅርስነት እንደተመዘገበ የተገለጸው፣ በሪያድ እየተካሔደ በሚገኘው 45ኛው የዓለም ቅርስ ኮሚቴ ጉባኤ ላይ ነው፡፡

የጌዴኦ ዞን ባህል እና ቱሪዝም መምሪያ፣ ምዝገባው፥ አካባቢውን ለማስተዋወቅ እንደሚረዳ ሲያመለክት፣ በጉዳዩ ላይ ተደጋጋሚ ምርምር ያደረጉት የዲላ ዩኒቨርሲቲ የአግሮ ኢኮሎጂ ፕሮፌሰር ታደሰ ክጴ በበኩላቸው፣ ቅርሱ በተሻለ ኹኔታ ተጠብቆ እንዲቆይ ያግዛል፤ ሲሉ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገረዋል።

የባሌ ተራሮዎች ብሔራዊ ፓርክም፣ ዛሬ ሰኞ፣ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት እንደተመዘገበ ታውቋል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።