ሀዋሳ —
ሲዳማ ክልል በመሆኑ ከደቡብ ክልል ተነጥሎ ብቻውን የቀረው ጌዴኦ ዞን የአደረጃጀት ጥያቄው የፍትሃዊ ተጠቃሚነትና የመልማት ጥያቄ ነው ሲሉ ምሁራን ተናገሩ።
በቡና ምርቱ የሚታወቀው የጌዴኦ ዞን ለደቡብ ክልልና ለሃገሪቱ የሚያበረክተው ከዞን አቅም ከፍተኛ ቢሆንም በአበረክቶው ልክ የኢኮኖሚና የፖሊቲካ ተጠቃሚ መሆን አልቻለም ብለዋል።
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ /ኢዜማ/ ጥያቄ ተገቢ መሆኑን ገልጦ ነገር ግን ወቅታዊነቱ መጤን እንዳለበት አሳስቧል።
ጥያቄው የህዝብ አይደለም በማለት የሚነሳውና ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚቀረበውን የሰላምና የፀጥታ ስጋት የዞኑ መንግሥት አስተባብሏል።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ የደቡብ ክልል የአደረጃጀት ጥያቄ ለመፍታት ሲባል የተለያዩ ጥናቶች መካሄዳቸውን ገልጠው ጥናቶቹ በተጨማሪ ምክረ ሃሳቦች እንዲዳብሩና ለውሳኔ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት መላኩን ሰሚኑን ገልፀዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5