የሙርሌ ታጣቂዎች እንደገና ማጥቃታቸውን ጋምቤላ ክልል አስታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

የሙርሌ ታጣቂዎች እንደገና ማጥቃታቸውን ጋምቤላ ክልል አስታወቀ

ከደቡብ ሱዳን ድንበር አቋርጠው ኢትዮጵያ ጋምቤላ ክልል የገቡ የሙርሌ ታጣቂዎች ትናንት ሦስት ሰዎችን መግደላቸውን፣ ሁለት የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን ማቁሰላቸውንና ሦስት ሕፃናትን አፍነው መውሰዳቸውን የክልሉ መንግሥት አስታውቋል።

የክልሉ ቃል አቀባይ አቶ ኡጌቱ አዲንግ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡጥ ቃል ታጣቂዎቹ ከታኅሣስ ወዲህ አሥራ ሦስት ሰዎችን መግደላቸውን በስደተኞች ላይ ጉዳት ሲያደርሱ ግን የአሁኑ የመጀመሪያ መሆኑን አመልክተዋል።