በጋምቤላ ከተማ እና ኢንታግ ወረዳ ግጭት ዘጠኝ ሰዎች ተገደሉ

Your browser doesn’t support HTML5

በጋምቤላ ከተማ እና ኢንታግ ወረዳ ግጭት ዘጠኝ ሰዎች ተገደሉ

በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ እና በጋምቤላ ከተማ በተቀሰቀሰ ግጭት፣ ዘጠኝ ሰዎች መገደላቸውን፣ የክልሉ ጸጥታ ቢሮ ምክትል ሓላፊ አቶ ኡቶዉ ኡኮት ተናግረዋል፤ በግጭቱ 17 ሰዎች መቁሰላቸውንም ገልጸዋል።

ግጭቱን ለማርገብ፣ የፌዴራል እና የክልሉ ባለሥልጣናት ተቀናጅተው እየሠሩ እንደኾነ፣ የክልሉ ፕሬዚዳንት ለአገር ውስጥ ብዙኃን መገናኛ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።