ችግኝ በመሸጥ 1.5 ሚሊየን ብር ገቢ ያገኘ ወጣት

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኛ የነበረው ዝናቡ ታከለ ችግኝ በማፅደቅ ሥራ

ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኝነት 1.5 ሚሊየን ብር ገቢ ወዳስገኘለት ችግኝ ተከላ የተሰማራ ወጣት በጋቢና ቪኦኤ የዘጋቢዎች መስኮት መሰናዶ ላይ እንግዳ ሆኗል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኛ የነበረው ዝናቡ ታከለ ያንን ሥራውን ትቶ ነሮውን በሰበታ እና ኦላንኮም ከተማ የኦዳን ችግኝ በማፍላትና በማከፋፈል ላይ የመሠረተ ወጣት ነው። በዚህ የክረምት ወቅት ብቻ ለሽያጭ ካቀረባቸው ሰላሣ ሺህ ችግኞች 1.5 ሚሊየን ብር ገቢ ያገኘው ወጣት ታከለ ሥራና የገቢ ምንጭ ከመፍጠሩ በተጨማሪ ኦዳን የማስተዋወቅ ዓላማም ነው ሰንቆ እየተንቀሳቀሰ ያለው።

ዘጋቢያችን ፀሐይ ዳምጠው ለጋቢና ቪኦኤ “የዘጋቢዎች መስኮት” መሰናዶ ዝርዝሩን አነጋግራዋለች።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

Your browser doesn’t support HTML5

ችግኝ በመሸጥ 1.5 ሚሊየን ብር ገቢ ያገኘ ወጣት