የስፓኝና የኢጣልያ የብድር ቁልል በዋስትና ሊከፈል ነው፤ አንጀላ መርከል አቋማቸውን ቀየሩ፡፡
ዋናዎቹ የአውሮፓ የኢኮኖሚ መሪ ሃገሮች የባንክ ሥርዓታቸውን ለማቀናጀትና የምጣኔ ኃብታቸውን ዕድገት ለማጠናከር የደረሱበትን ውሣኔና ያወጡትን መግለጫ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ አድንቀዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ይህንን አድናቆታቸውን ያሰሙት ሎስ ካቦስ ሜክሲኮ ለሁለት ቀናት የተካሄደው የሃያዎቹ ከበርቴ ሃገሮች ጉባዔ ትናንት ማምሻውን ሲጠናቀቅ ነው፡፡
“የዩሮ የገንዘብ ቀጣና በአንድነቱ እንዲቀጥል ለማድረግ ባሣዩት ዝግጁነት የጂ ሃያ ሃገሮች የዓለም ገበያዎችን ጭንቀት አርግበዋል፤ ለጥያቄዎቹም መልስ ሰጥተዋል” ብለዋል ፕሬዚዳንት ኦባማ፡፡
በጉባዔው ማብቂያ ላይ ከተነሡት ቁልፍ ጉዳዮች መካከል የዕድገትና የሥራ ዕድሎች መፈጠር ይገኙበታል፡፡
“ጂ ሃያ በአውሮፓ ቀውስ ተውጦ በማደግ ላይ ያሉ ሃገሮችን ጉዳይ ችላ ብሏል” የሚሉ ወቀሣዎች ቢሰሙም በሌላ በኩል ደግሞ “የቀሪውን ዓለም ችግሮች በተሻለ አያያዝ ለመፍታት እንዲቻል ለአውሮፓ ጉዳይ ቀዳሚ ትኩረት መሰጠቱ ትክክል ነው” የሚሉ ተንታኞችም አሉ፡፡
ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ፡፡
(ገፁ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ከማጫወቻዎቹ አንደኛውን ብቻ አስቀርተው የቀሩትን ያቁሟቸው፡፡)