በዩክሬን ሠርተው የከበሩት ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዩክሬናውያኑ የሰላም ተስፋ

Your browser doesn’t support HTML5

በዩክሬን ሠርተው የከበሩት ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዩክሬናውያኑ የሰላም ተስፋ

የሩሲያ የዩክሬን ወረራ፣ ዐያሌ ዩክሬናውያን አገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱ ከማስገደዱም በላይ ለብዙዎች ኅልፈት እና የንብረት ውድመት ምክንያት ኾኗል። ከሁለት ዓመት በላይ ያስቆጠረው ጦርነቱ፣ አሁንም እንደቀጠለ ነው።

የትግርኛ ክፍል ባልደረባችን ሣራ ፍሥሓየ፣ በአውሮፓ ጉዞዋ ወቅት፣ በጀርመን-ፍራንክፈርት ከተማ እና በአካባቢው የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዩክሬናውያንን አነጋግራለች።

ከሦስት ዐሥርት ዓመታት በላይ በዩክሬን ኖረዋል፤ ሀብት እና ልጆችም አፍርተዋል። ወግ ማዕርግ ከአዩባት ዩክሬን ጦርነቱን ሽሽት ድንገት እንደወጡ ሁለት ዓመት ያለፋቸው እኒኽ ቤተሰቦች፣ ወደ ዩክሬን የሚመለሱበትን ቀን በጉጉት ይጠባበቃሉ።

እስከ አሁን የጀርመን ሕዝብ እና መንግሥት ድጋፍ እያደረገላቸው የቆዩ ሲኾን፣ ለዚኽም አድናቆታቸውን ይገልጻሉ።

በጦርነት ዘለቄታዊ እልባት የሚያገኝ ግጭት እንደሌለ የሚናገሩት የቤተሰቡ አባላት፣ ችግሩን በንግግር ለመፍታት ይቻል ዘንድ፣ “የሩሲያ መንግሥት ከዩክሬን ለቆ መውጣት አለበት፤” ይላሉ።

ሙሉውን ፕሮግራም ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።