የፈረንሳይ ወታደራዊ ጦር ከሊብያ ወደ ቻድ የሚጓዙ መኪኖንች መለሰ

  • ቪኦኤ ዜና

FILE - This photo released Nov. 9, 2015, by the French Army shows a French Mirage 2000 jet on the tarmac of an undisclosed air base.

ከሊብያ ወደ ሰሜን ቻድ በሰልፍ ያመሩ የነበሩ 40 ፒክ-አፖ መኪናዋችን እንደመለሰ፣ የፈረንሳይ ወታደራዊ ጦር አስታወቀ።

የፈረንሳይ መከላከያ ሚኒስቴር በዛሬው ቀን እንዳስታወቀው፣ የተሸርካሪዎቹን ጉዞ ለመግታት /Mirage 2000/ ተዋጊ ጄቶችን ተጠቅሟል።

ጣልቃ-ገብነቱ የተካሄደው ከቻድ ባለሥልጣናት በቀረበ ጥያቄ መሠረት መሆኑን ያስታወቀው የፈረንሳይ ወታደራዊ ጦር፣ ዕርምጃውም "የጠላትነ" ያለውን አካሄድ ሊያስቀር እንደቻለም አመልክቷል።

ለዚህ ከሊብያ ለተንቀሳቀሰው የወረራ ጉዞ፣ ኃላፊነት የወሰደ ወገን አልቀረበም።