የፈረንሣዩ ፕረዚደንት ፍራንስዋ ኦላንድ በመጪው ማክሰኞ ዋሽንግተን መጥተው ከፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ጋር እስላማዊ መንግስት ነኝ የሚለውን ቡድን የመታገሉን ተግባር ስለማጠናከር ጉዳይ እንደሚወያዩ የዋት ሃውስ ቤተ መንግሥት መግለጫ ጠቁሟል። የፓሪሱን ጥቃት በማስከተል አሜሪካ በአይሲስ ላይ ከበፊቱ የከፋ ጫና እንደምታደርስም ቃል ገብታለች።
ዋሽንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚስተር ጆን ኬሪ ( John Kerry) አሜሪካ፣ ፈረንሣይና ሌሎች አጋር ሃገሮች እስላማዊ መንግሥት ነኝ በሚለው ቡድን ላይ የሚወስደው እርምጃ ከበፊቱ የከፋ ጫና እንደሚደርስበት ገልጸዋል።
አሸባሪው ቡድን ፓሪስ ላይ ለተፈጸሙ ጥቃቶች ሃላፊነት መውሰዱ የሚታወቅ ነው። ጆን ኬሪ ይህን የተናገሩት ከፈረንሣዩ ፕረዚደንት ፍራንስዋ (Francois Hollande)ኦላንድ ጋር ተገናኝተው ጽንተኛውን ቡድን በመዋጋት ረገድ መንግሥቶቻቸው የበለጠ ሥራ ስለሚሰሩበት ጉዳይ ከተነጋገሩበት በኋላ ነው። በጥቃቶቹ ብያንስ 129 ሰዎች እንደተገደሉ 300 የሚሆኑ ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው ይታወቃል።
የፈረንሣዩ ፕረዚደንት ፍራንስዋ ኦላንድ በመጪው ማክሰኞ ዋሽንግተን መጥተው ከፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ጋር እስላማዊ መንግስት ነኝ የሚለውን ቡድን የመታገሉን ተግባር ስለማጠናከር ጉዳይ እንደሚወያዩ የዋት ሃውስ ቤተ መንግሥት መግለጫ ጠቁሟል። ዘገባውን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል በመጫን ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5