አራት ጠፈርተኞች ከስድስት ወራት የጠፈር ቆይታ በኋላ ወደ ምድር ተመለሱ

ከፍሎሪዳ ባሕረ ገብ መሬት አቅራቢያ ከሚገኘው የሜክሲኮ ባሕረ ሰላጤ ላይ ያረፈችው የጠፈር መንኩራኩር፤ ፍሎሪዳ፣ እአአ መጋቢት 12/ 2024

ከፍሎሪዳ ባሕረ ገብ መሬት አቅራቢያ ከሚገኘው የሜክሲኮ ባሕረ ሰላጤ ላይ ያረፈችው የጠፈር መንኩራኩር፤ ፍሎሪዳ፣ እአአ መጋቢት 12/ 2024

ከአራት ሀገራት የተውጣጡ አራቱ ጠፈርተኞች ‘ስፔስኤክስ’ በተባለችው የጠፈር መንኩራኩር አማካኝነት በስድስተኛ ወራቸው ከዓለም አቀፉ የጠፈር ምርምር ጣቢያ ወደ ምድር ተመለሱ። በዩናይትድ ስቴትሱ የኤሮኖቲክስ እና የጠፈር አስተዳደር - ናሳ ተመራማሪዋ ጃስሚን ሞግቤሊ የተመራው የጠፈርተኞች ቡድን ከዴንማርክ፣ ከጃፓን እና ከሩሲያ የተውጣጡ ተመራማሪዎች ያሉበት ናቸው።

አራቱ ጠፈርተኞች 199 ቀናት ለወሰደው የጠፈር ምርምር ተልዕኳቸው ባለፈው የነሐሴ ወር ነበር ከምርምር ጣቢያው የገቡት። ተተኪዎቻቸው ባለፈው ሳምንት ከዓለም አቀፉ የጠፈር ምርምር ጣቢያ መድሳረቸው ተዘግቧል።

መንኩራኩራቸው ዛሬ ማክሰኞ ማለዳ ላይ ከፍሎሪዳ ባሕረ ገብ መሬት አቅራቢያ ከሚገኘው የሜክሲኮ ባሕረ ሰላጤ አርፋለች።