የቀድሞው የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት አህመድ ሲላንዮ አረፉ

የቀድሞው የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት አህመድ ሞሃመድ ሞሃሙድ ሲላንዮ

የቀድሞው የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት አህመድ ሞሃመድ ሞሃሙድ ሲላንዮ

የቀድሞው የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት አህመድ ሞሃመድ ሞሃሙድ ሲላንዮ ዛሬ አርብ በ88 ዓመታቸው ሃርጌሳ ውስጥ ማረፋቸውን የሶማሌላንድ ቴሌቭዥን አስታወቀ።

እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2010 በከፍተኛ የሕዝብ ድምፅ ለአምስት አመት የስልጣን ዘመን የተመረጡት ሲላንዮ፤ የሥራ ዘመናቸው ለተከሉት ሁለት ዓመታት ከተራዘመ በኋላ፤ በአሁኑ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ እስከ ተተኩበት እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር 2017 ድረስ አገልግለዋል።

እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ1982 የተመሰረተውን እና በኢትዮጵያ መንግስት ይደገፍ የነበረውን የሶማሌ ብሔራዊ ንቅናቄ የተቀላቀሉት ሲላንዮ የአማፂ ድርጅት መርተዋል። በመጀመሪያው የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት የቀድሞው አማጺ መሪ አብዲራህማን አሊ ቱር እስከተኩበት ጊዜ ድረስም አማጺ ቡድኑን ለበርካታ አመታት መርተዋል።

ሲላንዮ የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት በነበሩበት ወቅት ከሶማሊያ ፌዴራል መንግስት መሪዎች ጋር ውይይት ጀምረው ነበር። ከአሁኑ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ የመጀመሪያ የስልጣን ዘመን፤ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር 2014 አንስቶ በሁለቱ ወገኖች መካከል ተከታታይ ውይይቶች ቢካሄዱም፤ ጥረቶቹ በሙሉ ለስኬት ሳይበቁ ቀርተዋል።

የሲላንዮ ዜና እረፍት የተሰማው ሶማሌላንድ አራተኛውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ካካሄደች ሁለት ቀናት በኋላ መሆኑ ነው። የህልፈታቸው መንስኤ ይፋ አልተደረገም።

የቀድሞው የሶማሌላንድ መሪ የቀብር ሥነ ስርአታቸው ሰኞ እንደሚደሚፈጸም በዜና ዕረፍታቸው ተጠቅሷል።