ሂለሪ ክሊንተን በቤንጋዚው ግድያ ላይ የምስክርነት ቃላቸውን ሰጡ

የቀድሞዋ የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂለሪ ክሊንተን

የቀድሞዋ የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂለሪ ክሊንተን በመወሰኛው ምክር ቤት ምርመራ ኰሚቴ ፊት ቀርበው፣ በቤንጋዚ-ሊብያ ከየዩናይትድ ስቴትስሱ አምባሳደር ግድያ ጋር በተያያዘ የምስክርነት ቃላቸውን እየሰጡ ናቸው።

አምባሳደር ክሪስቶፈር እስቲቨንስ እና ሌሎች ሦስት አሜሪካውያን ዲፕሎማቶች በቤንጋዚ ሊብያ የተገደሉት፣ የቀድሞዋ የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂለሪ ክሊንተን በነበሩበት ጊዜ መሆኑ ይታወቃል።

ዛሬ ሂለሪ ክሊንተን በመወሰኛ ምክር ቤት ምርመራ ኰሚቴ ፊት ቀርበው ከዩናይትድ ስቴትስሱ አምባሳደር ግድያ ጋር በተያያዘ የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

የመርማሪው ኮሚቴ ሥራ ፖለቲካዊ አንደምታ እንዳለው ግልጥ ነው። ሊቀ-መንበሩ ቴሪ ጎዲ (Trey Gowdy) በእረጅሙ የመግቢያ ንግግራቸው ላይ እንዳስቀመጡት፣ ይህ ምርመራ ከነዚህ ቀደሞቹ የተለየና ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው ነው ብለዋል።

Your browser doesn’t support HTML5

ሂለሪ ክሊንተን በቤንጋዚው ግድያ ላይ የምስክርነት ቃላቸውን ሰጡ

ሊቀ-መንበሩ፣ እአአ ባለፈው መጋቢት ወር 2015 ዓ.ም. ይፋ የወጣውንና ለወራት ያህል ያወያየውን የክሊንተንን የኢሜል ውዝግብ አብረው ጠቅሰውታል። በዚህም፣ ክሊንተን በውጩ ጉዳይ ሚኒስትርነታቸው ወቅት የግል የኢሜይል ማደራጃ (private email server) ኰምፒውተር ተጠቅመዋል ነው የተባለው።

የአሜሪካ ድምፅ ጋዜጠኛ ጀፍ ካስተር ያዘጋጀውን ዝርዝር አዲሱ አበበ አቅርቦታል። የተያያዘውን የድምፅ ፋይል በመጫን ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ሂለሪ ክሊንተን በቤንጋዚው ግድያ ላይ የምስክርነት ቃላቸውን ሰጡ /ርዝመት -3ደ42ሰ/