ጆርጅ ደብሊው ቡሽ ለጆ ባይደን የእንኳን ደስ ያለዎ መልዕክት አስተላለፉ

  • ቪኦኤ ዜና
ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ደብሊው ቡሽ እና ባለቤታቸው ላውራ ቡሽ

ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ደብሊው ቡሽ እና ባለቤታቸው ላውራ ቡሽ

የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ሪፖብሊካን ፕሬዚዳንት ጆርጅ ደብሊው ቡሽ ባለፈው ሳምንት በተከናወነው ምርጫ ማሸነፋቸው ለተነገረላቸው ለዲሞክራቱ ጆ ባይደን የእንኳን ደስ ያለዎ መልዕክት አስተላልፈዋል።

"ተመራጩ ፕሬዚዳንት ሃገራችንን የመምራት እና አንድ የማድረግ ዕድል አሸናፊ ሆነዋል" ብለዋል ጆርጅ ቡሽ።

እአአ ከ2001 እስከ 2009 ሃገሪቱን የመሩት ቡሽ "ከባይደን ጋር የፖለቲካ ልዩነቶች አሉን፤ የሆነ ሆኖ በሥራቸው ስኬት እንዲያገኙ እፀልይላቸዋለሁ። በምችለው ሁሉ ልረዳቸው ቃል እገባለሁ" ብለዋል።

ተመራጯን ምክትል ፕሬዚዳንት ካምላ ሃሪስንም የቀድሞው ፕሬዚዳንት ቡሽ እንኳን ደስ ያለዎ ብለዋል።