ለመናገርና ለመስማት የሚከብድ ዘግናኝ ተግባር ተፈጽሞብኛል

ዮናስ ጋሻው

ዮናስ ጋሻው ደመቀ ባለፈው ሣምንት ከእስር የተፈታ ወጣት “በተፈፀመብኝ ለመናገርና ለመስማት የሚከብድ ኢሰብዓዊ ሥቃይ ዛሬ ከዊልቸርና ክራችስ (ከወንበርና ከምርኩዞች) ውጪ ራሴን ችዬ መንቀስቅቀስ የማልችል ሰው ሆኛለሁ” ይላል። (ጽዮን ግርማ በተከታዩ ዘገባ ታሪኩን ይዛለች።)

Your browser doesn’t support HTML5

ለመናገርና ለመስማት የሚከብድ ዘግናኝ ተግባር ተፈጽሞብኛል

ዮናስ ጋሻው በቅርቡ ከእስር የተፈታ ወጣት ነው። “በሁለት እግሬ ገብቼ በምርኩዝ ወጣሁ” ይላል ታሪኩን ሲናገር። ተወልዶ ያደገው ፍኖተ ሰላም ነው። በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ትምህርቱን አጠናቆ አንድ ዓመት እንደሠራ ጥር 4 ቀን 2009 ዓ.ም ለእስር መዳረጉን ይናገራል። ባለትዳርና የአንዲት የሁለት ዓመት ከስምንት ወር ልጅ አባት ነው።

“አዲስ አበባ ውስጥ ሳሪው አካባቢ ከእህቶቹ ጋራ በታክሲ እየሄድን በፌደራል ፖሊስና በመከላከያ መኪና ወደ ዐሥራ ሁለት በሚጠጉ ሰዎች ተከበን ተይዤ ተወሰድኩ” ይላል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ)