የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትሮች በአዲሱ ላይ...

የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትሮች

ጠቅላይ ሚኒስትር በሕግ የተደነገገ ሥራ ቢኖረውም ሁሉም ጥቅል ነውና መንግሥቱ የሚፈፅማቸውን ተግባራት ዝርዝር እያበጀ ሃገር ያስተዳድራል፤ ሕዝብን ይመራል።

አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ‘ይህን ይህን እንዲሠሩ ወይም እንዲሠሩልን እንፈልጋለን፤’ የሚሉ ዜጎች፣ የዜጎች ማኅበራትና ስብስቦች፣ ዓለምአቀፍ ተቋማትና የመብቶች ተሟጋቾች ቁጥራቸው ብዙ ነው።

ለመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ ምን ማለት ይሆን?

ከዚህ ጋር የተያያዙት የድምፅ ፋይሎች ከሁለት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትሮች ጋር የተደረጉ ቃለ-ምልልሶችን ይዘዋል።

በደርግ ዘመን ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ እና ከደርግ በኋላ ደግሞ በሽግግሩ ዓመታት ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ኢሕአዴግ መንግሥቱን ሲያቆም ደግሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉት አቶ ታምራት ላይኔ የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ቃለ-መሃላ ከመፈፀማቸው አንድ ቀን ቀደም ብሎ ከቪኦኤ ጋር ባደረጓቸው በእነዚህ ቃለ-ምልልሶች አዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትር የሚጠብቋቸው ፈተና እጅግ ከባድ እንደሚሆኑ በየግላቸው ተናግረዋል።

ምንም እንኳ ሁለቱም የቀድሞ ባለሥልጣናት ቢሮዎቻቸው የዋና ሥራ አስፈፃሚ ቀጥተኛ ኃላፊነትና ተግባር አይኑሯቸው እንጂ ሥራውን ለማወቅ ከእነርሱ የቀረበ አልነበረምና ተሞክሮዎችና ምክሮቻቸው የግንባር ወይም የመስክ ናቸው ማለት ይቻላል። ያዳምጧቸው።

Your browser doesn’t support HTML5

ሻ/ል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ሰለ ዶ/ር አብይ አሕመድ

Your browser doesn’t support HTML5

አቶ ታምራት ላይኔ ሰለዶ/ር አብይ አሕመድ - ክፍል 1

Your browser doesn’t support HTML5

አቶ ታምራት ላይኔ ስለዶ/ር አብይ አሕመድ - ክፍል 2