በኢህአዴግ መንግሥትና መከላከያ ሰራዊት ውስጥ ጉልህ ስፍራ የነበራቸው መኮንኖች በዛሬው ዕለት ከዝዋይና ቃሊቲ ማረሚያ ቤቶች መለቀቃቸው ታውቋል፡፡
ዋሺንግተን ዲሲ —
በኢህአዴግ መንግሥትና መከላከያ ሰራዊት ውስጥ ጉልህ ስፍራ የነበራቸው መኮንኖች በዛሬው ዕለት ከዝዋይና ቃሊቲ ማረሚያ ቤቶች መለቀቃቸው ታውቋል፡፡
ከሥምንት ዓመት በላይ ታስረው ዛሬ ከተፈቱት መካከል፣ ጀነራል ተፈራ ማሞ፣ ጀነራል አሳምነው ፅጌ፣ ኢንጂነር መንግሥቱ አበበ፣ ኮሎኔል ደምሰው አንተነህ፣ ኮለኔል አበረ አሰፋ፣ ኮለኔል ሰለሞን አሻግሬ፣ ሻለቃ መኮንን ወርቁ፣ ሻለቃ መሰከረ ካሳ፣ ሻለቃ ምስጋናው ተሰማ፣ ኢኒስፔክተር አመራር ባያብል፣ ነርስ የሸዋስ ማንገሻ፣ ዋና ሳጅን ጎበና በላይ፣ ሳጅን ይበልጣል ብራሃኑ እና ሌሎች እስረኞች ይገኛሉ፡፡
በቅርብ እስረኞቹን በማነጋገር ዘገባ እናቀርባለን፡፡