በአፍሪካ እግር ኳስ ታሪክ ትቅል ስፍራ የነበራቸው ቀድሞው የፊፋ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት እና የረጅም ጊዜ የአፍሪካ እግር ኳስ መሪ ኢሳ ሀያቱ በ77 ዓመታቸው ፓሪስ ውስጥ ትላንት ሀሙስ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።
የወቅቱ የፊፋ ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ በኢንስታግራም ገፃቸው ላይ “የቀድሞው የካፍ ፕሬዝዳንት፣ የፊፋ ጊዚያዊ ፕሬዝዳንት እና የፊፋ ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም የፊፋ ምክር ቤት አባል ኢሳ ሀያቱ በማለፋቸው አዝኛለሁ" ብለዋል፡፡
የ2024 ኦሎምፒክ ጨዋታዎች እየተካሄደባት ባለችው ፓሪስ ያረፉት ሀያቱ ለስፖርት ስለነበራቸውም ፍቅር የገለጹት ፕሬዚዳንቱ “ስፖርት አፍቃሪ ህይወቱን ለስፖርት አሳልፏል። በፊፋ ስም ለቤተሰቦቹ፣ ለጓደኞቹ፣ ለቀድሞ ባልደረቦቹ እና ለሚያውቋቸው ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን” ሲሉ አክለዋል፡፡
ስፖርት አፍቃሪ ህይወቱን ለስፖርት አሳልፏል። በፊፋ ስም ለቤተሰቦቹ፣ ለጓደኞቹ፣ ለቀድሞ ባልደረቦቹ እና ለሚያውቋቸው ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን”
ሀያቱ እ.ኤ.አ. በ2015 የሙስና ቀውስ ውስጥ ገብቶ ለነበረው ፊፋ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት በመሆን ያገለገሉ ሲሆን የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የረዥም ጊዜ መሪ በመሆን እስከ 2017 ድረስ ለ29 ዓመታት መርተዋል፡፡
ሀያቱ የዓለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ለ15 ዓመታት ያገለገሉ ሲሆን ከዚያም በኋላ የኮሚቴው የክብር አባል በመሆን ቆይተዋል፡፡
ትውልደ ካሜሩኑ ሀያቱ ምንም እንኳ የታወቁት በአትሌክሱ የሩጫ መድረክ ሻምፒዮንነታቸው ቢሆንም በሀገራቸው የገነኑት በእግር ኳስ ጨዋታ ነው፡፡
እ.ኤ.አ. በ2002 ከሴፕ ፕላተር ጋር ለፊፋ ፕሬዝዳንትነት በተወዳደሩበት ወቅት የአውሮፓውያንን ድጋፍ ቢያገኙም በምርጫው ድል አልቀናቸውም።
ስመጥር ከሆነ ካሜሩናውያን ቤተሰብ እንደተወለዱ የተነገረላቸው ሀያቱ ወንድማቸው ሳዱ ሀያቱ እኤአ ከ1991 እስከ 1992 የካሜሩን መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ማገልገላቸውን አሶሴይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡