ዋሺንግተን ዲሲ —
የማሊ የቀድሞ ፕሬዚዳንት አማኒ ቱማኒ ቱሬ በሰባ ሁለት ዓመታቸው አረፉ።
የቀድሞው ፕሬዚዳንት ቱርክ ውስጥ እንዳረፉ ነው ሮይተርስ ሲገልፅ፣ የህልፈታቸው ምክንያት አልተገለጸም።
የቀድሞ የጦር ሰራዊት ጀነራል የነበሩት ፕሬዚዳንቱ ምርጫዎች ማደራጀትን ጨምሮ በማሊ የዲሞክራሲ ለውጥ ለማካሄድ ባደረጓቸው ጥረቶች ይወደሳሉ።
የማሊ የቀድሞ ፕሬዚዳንት አማኒ ቱማኒ ከስምንት ዓመታት በፊት በመፈንቅለ መንግሥት የተወገዱ ሲሆን ከእርሳቸው በኋላ በትረ ሥልጣኑን የጨበጡት ኢብራሂም ቡባካርም ከሦስት ወራት በፊት በፈንቅለ መንግሥት እንደወረዱ ይታወሳል።