ከመንፈቅ ዓመቱ የእሳት አደጋዎች 94 በመቶ በአዲስ አበባ የደረሱ ናቸው

Your browser doesn’t support HTML5

ከመንፈቅ ዓመቱ የእሳት አደጋዎች 94 በመቶ በአዲስ አበባ የደረሱ ናቸው

በኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ በደረሰው የእሳት አደጋ ወደ ግማሽ ቢሊዮን ብር ንብረት መወደሙ ተገለጸ።

በዚህ ዓመት ስድስት ወራት ውስጥ 139 የእሳት ቃጠሎዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ መድረሳቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የተናገሩት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጄይላን አብዲ፣ መንሥኤያቸውንም በፎረንሲክ ምርመራ ለመለየት እንደተቻለ ገልጸዋል።

ከእሳት ቃጠሎዎቹ 94 በመቶዎቹ በአዲስ አበባ መድረሳቸውን የጠቀሱት የእሳት እና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ባለሞያ አቶ ንጋቱ ማሞ፣ ግማሽ ቢሊዮን ብር ገደማ ሀብትም በአደጋው መውደሙን ተናግረዋል።

በጉዳዩ ላይ፣ ዘጋቢያችን በቅርቡ በእሳት ቃጠሎ ቤታቸው የወደመባቸውን የአዲስ አበባ ነዋሪንም አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ አዘጋጅቷል፡፡