የፊደል ካስትሮ ልጅ ራሳቸውን አጠፉ

  • ቪኦኤ ዜና

ፎቶ ፋይል:- ፊደል ካስትሮ ዲያዝ ባላርት

የኩባው ኮምኒስት መሪ የፊደል ካስትሮ ልጅ ትናንት ሐሙስ ራሳቸውን ማጥፋታቸው ተነገረ።

የኩባው ኮምኒስት መሪ የፊደል ካስትሮ ልጅ ትናንት ሐሙስ ራሳቸውን ማጥፋታቸው ተነገረ። ሰበቡ፣ ለወራት ያህል በከፍተኛ ድብርትና የመንፈስ ጭንቀት ውስጥ መክረማቸው ነው ተብሏል። ዕድሜያቸውም 68 ነበር።

አባታቸውን ይመስሉ ስለነበር ፊደሊቶ «ትንሹ ፊደል» ይባሉ የነበሩት ፊደል ካስትሮ ዲያዝ ባላርት፣ በቀድሞዋ ሶቭዬት ሕብረት ኒዩክለር ፊዚክስ አጥንተው፣ ኩባ ውስጥ የመንግሥቱ ምክር ቤት አማካሪ ነበሩ።

ፊደል ካስትሮ ዲያዝ ባላርት፣ የኩባ ሳይንስ አካዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት ሆነው ከማገልገላቸውም በላይ፣ እአአ ከከ1980-1992 ፣ የኩባን የኑክሊየር ፕሮግራም በበላይነት መርተዋል።