አምባሳደር ፌልትማንና ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር መወያየታቸውን የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ትናንት በሰጡት መግለጫ፣ ለሁለት ቀናት ጉብኝት በትናንትናው ዕለት አዲስ አበባ የገቡት የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን በትናንትናው የአዲስ አበባ ቆይታቸው ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ ከመከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ እና ከገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ጋር እንደተወያዩ አስታውቀዋል፡፡
የጉብኝታቸው ዓላማ በኢትዮጵያ እየተስፋፋ ላለው ግጭት መፍትሔ ማፈላለግ ላይ ያተኮረ እንደሆነም ኔድ ፕራይስ አስታውቀዋል። ለዚህም መሳካት ሁሉም አካላት ነፍጣቸውን እንዲያወርዱ እና ግጭት እንዲያቆሙ ዩናይትድ ስቴትስ መጠየቋን አሁንም ስለመቀጠሏ አንስተዋል፡፡
አምባሳደር ፌልትማን ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር መወያየታቸውን የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ለሁለት ቀናት ጉብኝት በትናንትናው ዕለት አዲስ አበባ የገቡት የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን፣ ትናንት በነበራቸው ቆይታ አቶ ደመቀ መኮንንን ጨምሮ ከሶስት ከፍተኛ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር መወያየታቸውን የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ
Your browser doesn’t support HTML5