የሰማዕታት ቀን እና የኢትዮጵያውያን የወቅቱ አቤቱታ

አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

የዛሬ 80 ዓመት፣ የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም፣ በአዲስ አበባ 30 ሺኽ ኢትዮጵያውያን በግፍ ተገድለዋል። ዕለቱም የሰማዕታት መታሰቢያ ቀን ይባላል።

የዛሬ 80 ዓመት፣ የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም፣ በአዲስ አበባ 30 ሺኽ ኢትዮጵያውያን በግፍ ተገድለዋል። ዕለቱም የሰማዕታት መታሰቢያ ቀን ይባላል። የዘንድሮው 80ኛ ዓመት ነው። የፊታችን እሑድ የሚታሰበውን ይህን የሰማዕታት ቀን ከኢትዮጵያ ውጪ የሚገኙ ኢትጵያውያን በተለያዩ ዝግጅቶች ያስታውሱታል። ከእነዚህ አንዱ፣

"ዓለማቀፍ ሕብረት ለፍትህ የኢትዮጵያ ጉዳይ" የተሰኘው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ነው።

ለእነዚህ በግፍ ለተገደሉ ኢትዮጵያውያን ምንድነው የሚጠየቀው?

ምን ዓይነት ፍትህ ነው የሚፈለገውስ?

80ኛውን የየካቲት 12 የሰማዕታት ቀን፣ በማስታወስ እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ እና አውሮፓ ጭምር ዝግጅት ያደረገው የድርጅቱ አባላት፣ እነዚህን ጥያቄዎች በመመለስ የዛሬው ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ ፕሮግራማችን እንግዶች ይሆናሉ።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የሰማዕታት ቀን እና የኢትዮጵያውያን የወቅቱ አቤቱታ