ፌክ ኒውስ - የፈጠራ ወሬ፡- ምንጩ፣ መገለጫው፣ መዘዙ፣ ማርከሻው...

አቶ ዳኛቸው ተሾመ

የፈጠራ ወሬ ወይም FAKE NEWS አንባቢን ወይም አድማጭን ለማታለል ወይም ትክክለኛ መረጃ እንዳያገኝ ሆን ተብሎ የሚሠራጭ አሳሳችና የሃሰት ዜና ነው። የባለሙያ ትንታኔ ይዘናል።

FAKE NEWS ወይም የፈጠራ ወሬ በተለይ አሁን አሁን ብዙ አድማጭና አንባቢ ከሚታወቁ የዜና ማሠራጫ ጣቢያዎች ይልቅ ከተለያዩ ማኅበራዊ መገናኛዎች ዜና በሚፈልግበት፣ በሚቃርምበትና ሃሣቡንም በሚያንሸራሽርበት ዘመን አደጋው ከፍተኛ ሆኗል።

FAKE NEWS ወይም የፈጠራ ወሬ በማኅበረሰብ ውስጥ መተማመንን ያሳጣል፤ መንግሥትና ሕዝብን፣ ሕዝብን ከሕዝብ ያጋጫል።

በFAKE NEWS ወይም በፈጠራ ወሬ ሥርጭት ላይ ጥናት ያደረጉ ማርከሻውንም የሚመክሩ ባለሙያ አቶ ዳኛቸው ተሾመ ለጥያቄዎችዎ መልስ ይሰጣሉ።

አቶ ዳኛቸው ተሾመ ሎስ አንጀለስ - ካሊፎርኒያ የሚኖሩ ላለፉት ሰላሣ ዓመታት በትምህርት፣ በምርምርና በሥራም ከኮምፕዩተር ሳይንስ ጋር ያሉ ሰው ናቸው። በዳታ ቤዝ ዲዛይንና አርክቴክቸር ላይ ሠርተዋል። የሁለተኛ ዲግሪያቸውን ምርምርና ፅሁፍም የሠሩት ድምፅን በመፈተሽና ለይቶ በማወቅ ክህሎት ላይ መሆኑን ይናገራሉ። ከዚያ በተለይ ግን አቶ ዳኛቸው እራሴን ማሳወቅ የምፈልገው “ሕይወቱን ለሰው ልጅ መብት መከበር እንደሰጠ ሰው ነው” ይላሉ።

የጄነራል አሳምነው ፅጌና የአማራ ክልል መገናኛ ብዙኃን ኃላፊ የመጨረሻ የስልክ ምልልስ የድምፅ ቅጂም ዩናይትድ ስቴትስ በሚገኝ ዲጂታል አሻራ መርማሪ ቡድን አስመርምረው ያገኙትን ውጤትም ያካፍላሉ።

ከተያየዘው የድምፅ ፋይል ሙሉውን ዝግጅት ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ፌክ ኒውስ - የፈጠራ ወሬ፡- ምንጩ፣ መገለጫው፣ መዘዙ፣ ማርከሻው...

የዲጂታል አሻራ መርማሪ ባለሙያዎች /ዲጂታል ፎረንሲክ ኤክፐርትስ/ ድርጅት ሪፖርት ከሥር ሠፍሯል /ይመልከቱት/

1 t is the professional opinion of Digital Forensic Experts that the reporter and the deceased person, now referred to as “speaker”, were recorded at the same time, or possibly Re-recorded at the same time. There is a continuous ENF present (Electrical Network Frequency). This signal is unbroken, signifying that on the recording we have been supplied, the reporter and the speaker were recorded simultaneously. Alternatively, the speaker’s recording could have been played back while the reporter inserted his dialogue at the appropriate times thus creating the unbroken ENF. The reporter’s voice was not “spliced together” with that of the speaker.

ይህ የዲጂታል ፎረንሲክ ኤክስፐርትስ - የድርጅቱ ስም ነው - /ዲጂታል አሻራ መርማሪ ባለሙያዎች/ ሙያዊ አስተያየት ነው። ሪፖርተሩና ሟቹ /አሁን “ተናጋሪው” የሚባሉት/ የተቀረፁት በአንድ ጊዜ /በተመሣሣይ ጊዜ ወይም አንድ ላይ/ ነው፤ ወይም /የሁለቱም ድምፅ/ እንደገና ተቀርፆም ከሆነ የተቀረፀው በአንድ ጊዜ /ወይም አንድ ላይ/ ሊሆን ይችላል። ያልተቋረጠ /ወይም የተያያዘና ተከታታይ/ ኢ.ኤን.ኤፍ. - የእንግሊዝኛ አባባል ምኅፃር ነው - የኤሌክትሪክ ትስስር /ኔትወርክ/ ሞገድ አለ። የድምፁ ሂደት የተሰባበረ አይደለም፤ ይህ ማለት ለእኛ በተላከልን የተቀረፀ ድምፅ ላይ ሪፖርተሩና ተናጋሪው የተቀረፁት በአንድ ጊዜ /በተመሣሣይ ጊዜ ወይም በአንድ ላይ/ መሆኑን ያረጋግጣል። በሌላ በኩል ደግሞ የኤሌክትሪክ ትስስር ሞገዱ /ኢ.ኤን.ኤፍ/ እንዳይቆራረጥ ለማድረግ ሪፖርተሩ መጠይቆቹን ተገቢ ጊዜያቸውን እየጠበቀ የተናጋሪውን ቀድሞ የተቀረፀ ድምፅ እያጫወተ ቀርፆ ሊሆንም ይችላል። የሪፖርተሩ ድምፅ ከተናጋሪው ድምፅ ጋር እየተቆራረጠ አልተቀጣጠለም።

2. It is the professional opinion of Digital Forensic Experts that the source has not been manipulated. There are no tell-tale signs of editing, including crossfades, inconsistent waveforms, clips or other anomalies.

ይህ የዲጂታል ፎረንሲክ ኤክስፐርትስ - የድርጅቱ ስም ነው - /ዲጂታል አሻራ መርማሪ ባለሙያዎች/ ሙያዊ አስተያየት ነው። ምንጩ ላይ ለማስተካከል ወይም ለመቀማመር ተብሎ በእጅ የተከናወነ ሥራ የለም። አንዱን ድምፅ በሌላኛው ላይ ማስኬድን፣ ወጥነት የሌላቸው የድምፅ ውጣ ውረድ ዓይነቶችን፣ ቆርጦ መቀጠልን ወይም መሰል ለማጭበርበር ተብሎ የተፈፀመ የአርትኦት ሥራ የለበትም።

3. Finally, It is the professional opinion of Digital Forensic Experts that the speakers voice in the reporter recording and the two sample recordings match. Please see the spectrograms of audio fingerprint with the significant frequencies circled. There are other background frequencies mixed in and a speakers voice has minor changes from day to day, but the main points exist, as well as the space between the key frequencies.

በመጨረሻም ሪፖርተሩ ያወጣው የተቀረፀ ድምፅና የቀረቡት ሁለት ናሙናዎች ተመሣሣይ /ወይም አንድ/ መሆናቸውን የዲጂታል ፎረንሲክ ኤክስፐርትስ - የድርጅቱ ስም ነው - /ዲጂታል አሻራ መርማሪ ባለሙያዎች/ ሙያዊ አስተያየት ያረጋግጣል። የተቀረፀውን ድምፅ አሻራ የያዘውን ድምፅ በጊዜ ውስጥ የሚያሳየውን ሞገድ ሂደት የሚያመላክቱ ምሥሎች /ስፔክቶግራምስ/ በተለይ የተከበቡትን ሞገዶች ይመልከቱ። ከተናጋሪው ድምፅ ጋር የተቀላቀሉ ሌሎች የጀርባ የድምፅ ሞገዶች ከጊዜ ወደ ጊዜ አነስተኛ ለውጦችን ቢያሳዩም ዋናዎቹ ነጥቦች፣ እንዲሁም ቁልፍ በሆኑት ሞገዶች መካከል ያሉት ክፍተቶች ግን አሉ።