በዛሬው ፍንዳታ ሰባት ሰዎች ሲገደሉ፣ ከሞቱት ውስጥ አምስቱ አጥቂዎችን እንደሚጨምር ታውቋል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
በኢንዶኔዥያዋ ዋና ከተማ ጃካርታ ውስጥ በተቀነባበረ መንገድ ለተካሄደውና፣ ሰባት ሰዎች ለተገደሉበት የቦምብ ፍንዳታ፣ እራሱን እስላማዊ መንግሥት የሚለው ነውጠኛ ቡድን ኃላፊነት መውሰዱ ተገለጸ።
ሰባት ሰዎች የተገደሉት የዛሬው ፍንዳታ፣ አምስቱን አጥቂዎችም እንደሚጨምር ታውቋል።
ከእስላማዊው መንግሥት ነኝ ከሚለው ቡድን ጋር ትስስር ያለው አማክ (Aamaq) የዜና አገልግሎት እንደዘገበው፣ ፍንዳታው ዒላማ ያደረገው የውጪ አገር ዜጎችንና የፀጥታ ኃይሎችን ነበር።
ቀደም ሲል የኢንዶኔዥያ ብሔራዊ ፖሊስ መምሪያ ቃል-አቀባይ አንተቶን ቻርልያን (Anton Charliyan) ሲናገሩ፤ ከግድያው ኋላ የአይስስ (ISIS) እጅ እንዳለበትና ነውጠኞቹም የፓሪሱን የመሰለ የሽብርተኞች ጥቃት የመሰለ ለመድገም እንደሞከሩ ገልጸዋል።