በፍንዳታው እስካሁን የሞተ ሰው እንደሌለ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ የጀመሩትን ለውጥ ለማበረታት በተጠራው በዛሬ ሰልፍ ላይ በእጅ ቦንብ 98 ሰዎች መቁሰላቸውን እስካሁን ግን ሕይወቱ ያለፈ ሰው ሪፖርት አለመደረጉን ፌደራል ፖሊስ ለአሜሪካ ድምፅ አስታወቀ። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማልን አነጋግረናቸዋል።