ብሪታንያ ከሀገሯ እንዲወጡ ያዘዘቻቸው የሩሲያ ዲፕሎማቶች

  • ቪኦኤ ዜና
ብሪታንያ ከሀገሯ እንዲወጡ ያዘዘቻቸው የሩስያ ዲፕሎማቶች ለመውጣት እይተዘጋጁ ናቸው።

ብሪታንያ ከሀገሯ እንዲወጡ ያዘዘቻቸው የሩስያ ዲፕሎማቶች ለመውጣት እይተዘጋጁ ናቸው።

ዲፕሎማቶቹ ውጡ የተባሉት በቀድሞ የሩስያ ሰላይ ላይ እና ሴት ልጃቸው ላይ ብሪታንያ ውስጥ ከደረሰው ነርቮች ላይ ጉዳት የሚያደርስ መርዝ በተያያዘ ነው።

ዛሬ ለንደን የሚገኘው የሩስያ ኤምባሲ ደጃፍ፣ ዕቃ ማጓጓዣ መኪና መታየቱን የሩስያ የዜና ማሰራጫዎች ዘግበዋል።

ሰርጌይ ስክሪፓል የሚባሉት የቀድሞ የሩስያ ሰላይ እና ልጃቸው ዩሊያ ሶልስበሪ የምትባል ከተማ ውስጥ መርዝ ያቀመሰቻቸው ሩስያ ናት ብላ ብሪታንያ ወንጅላታለች።

ሩስያም በበኩሏ በአፀፋው ሃያ ሦስት የብሪታንያ ዲፕሎማቶችን እንዲወጡ አዛለች፣ ውንጀላውንም አስተባብላለች፡፡