ሞክታር ኡዌን የማሊ የሽግግሩ ጠ/ሚ ሆነው ተሾሙ

  • ቪኦኤ ዜና

የቀድሞ የማሊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞክታር ኡዌን የሽግግሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ መሾም ባለፈው ወር ፕሬዚዳንቱን ኢብራሂም ቡባካር ኬይታን መንግሥት መገልበጥ ተከትሎ ማዕቀብ የጣለባት የምዕራብ አፍሪካ ሃገሮች የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ኤኮዋስ ካስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች መካከል አንዱ መሆኑ ታውቋል።

የቀድሞውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ትናንት እሁድ የሰየሟቸው ሥልጣን የያዘው ወታደራዊ ኮሚቴ የሽግግር ፕሬዚዳንት ያደረጋቸው ባህ ንዳው ናቸው።

የመፈንቅለ መንግሥቱ መሪ ኢሳም ጎይታ ምክትል ፕሬዚዳንትነቱን ይዘዋል።