የትረምፕ መመረጥ ኔቶ እና አውሮፓ ላይ ምን አንድምታ ይኖረዋል?

  • ቪኦኤ ዜና

የኔቶን አርማ የሚያሳዩ ባነሮች የኔቶ ዋና መሥሪያ ቤት መግቢያ በር ላይ ተቀምጠዋል፣ ብራስልስ፣ ቤልጂየም

Your browser doesn’t support HTML5

የትረምፕ መመረጥ ኔቶ እና አውሮፓ ላይ ምን አንድምታ ይኖረዋል?

አውሮፓዊያኑ የዩናይትድ ስቴትስ አጋሮች ዶናልድ ትረምፕ መመረጣቸው በጸጥታ እና ኢኮኖሚያቸው ላይ ምን ዓይነት አንድምታ እንደሚኖረው እየተነጋገሩ ናቸው፡፡ የመጀመሪያው የትረምፕ አስተዳደር ዘመን ከአውሮፓ ኅብረት እና ከሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ ) አባል ሀገሮች ጋራ በተደጋጋሚ በጎላ አለመግባባት የታየበት ነበር፡፡

የአሜሪካ ድምጹ ሄንሪ ሪጅዌል ሩስያ ዩክሬይን ላይ የከፈተችው ወረራ ስለውቂያኖስ ተሻጋሪው ኅብረት የአውሮፓ ሀገሮች ያላቸውን ስጋት ይበልጡን ያጎላው መሆኑን ጠቅሶ ከለንደን ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል፡፡