የአውሮፓ መሪዎች - ሩሲያ እአአ በ2014 ዓም የኡክሬንን ክሪሚያ ባህረገብ መሬት በመውረሯ የጣሉትን ማዕቀብ ለማራዘም ተስማምተዋል። መሪዎቹ ዛሬ ባወጡት መግለጫ - ማዕቀቡ የተራዘመው ለቀጣዮቹ 6 ወራት ነው ብለዋል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
የአውሮፓ መሪዎች - ሩሲያ እአአ በ2014 ዓም የኡክሬንን ክሪሚያ ባህረገብ መሬት በመውረሯ የጣሉትን ማዕቀብ ለማራዘም ተስማምተዋል። መሪዎቹ ዛሬ ባወጡት መግለጫ - ማዕቀቡ የተራዘመው ለቀጣዮቹ 6 ወራት ነው ብለዋል።
የአውሮፓ መሪዎች ኡክሬንን አስመልክቶ አጭር ውይይት ካደረጉ በኋላ ከዚህ ውሳኔ የደረሱት በብራሰልሱ ስብሰባቸው ላይ መሆኑን አንድ ማንነቱ ያልተገለፀ ምንጭ ለፈረንሳይ የዜና አገልግሎት ተናግሯል።
ዩናይትድ ስቴትስም በዚሁ ሳቢያ በሩሲያ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ማቆየት እንደምትፈልግ ተዘግቧል።
ሩሲያ በ2016ቱ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዶናልድ ትረምፕ እንዲያሸንፉ ለመርዳት እጇን አስገብታለች ብለው እንደሚያምኑ - የሃገሪቱ የደኅንነት ጥበቃ መሥሪያ ቤቶች አስታውቀዋል።
ሞስኩ በምርጫው ጣልቃ አልገባችም ሲሉ በቅርቡ ከሩሲያው አቻቸው ጋር እንደሚገናኙ የተገለጸው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይከራከራሉ። ይህንኑ ለመመርመር የተቋቋመውን ልዩ አካልም እያንቋሸሹት ይገኛሉ።