ሠላሳ ዘጠኝ የአውሮፓ ፓርላማ አባላት የኢትዮጵያ የሠብዓዊ መብቶች ሁኔታ ያሳሰባቸው መሆኑን የሚገልፅ ደብዳቤ ለአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳዮችና የፀጥታ ከፍተኛ ተጠሪ እንዲሁም ለሕብረቱ ኮሚሽን ምክትል ፕሬዘዳንት ለሆኑት ለፌዴሪካ ማግሪኒ አቅርበዋል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ሠላሳ ዘጠኝ የአውሮፓ ፓርላማ አባላት የኢትዮጵያ የሠብዓዊ መብቶች ሁኔታ ያሳሰባቸው መሆኑን የሚገልፅ ደብዳቤ ለአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳዮችና የፀጥታ ከፍተኛ ተጠሪ እንዲሁም ለሕብረቱ ኮሚሽን ምክትል ፕሬዘዳንት ለሆኑት ለፌዴሪካ ማግሪኒ አቅርበዋል።
ይኸው የምክር ቤት አባላቱ ፊርማቸውን ያኖሩበት ደብዳቤ የኢትዮጵያ መንግሥት የኦሮሞዎችን ተቃውሞ በሃይል ለመጨፍለቅ በወሰደው ዕርምጃ የተገደሉት ሰዎች ጉዳይ በነፃ አካል እንዲመረመር የአውሮፓ ፓርላማ ባለፈው ግንቦት ያሳለፈውን ውሳኔ አጉልቶ ያሳያል።
የመንግሥቱ የፀጥታ ኃይሎች በተቃዋሚ ሰልፈኞቹ ላይ የኃይል ዕርምጃ ከመውሰዳቸውም በላይ በመላ ሃገሪቱ ዙሪያ በሚገኙ አነስተኛ ቁጥር ባላቸው ብሄረሰቦች ሴቶች ላይ አስገዳጅ ወሲብ ፈፅመዋል የሞት ፍርድ የተበየነበትን የብሪታንያ ዜግነት ያለውን አንዳርጋቸው ፅጌን ጨምሮ የፖለቲካ መሪዎችን ማሠራቸውን ቀጥለዋል ሲል ይከሳል።
ደብዳቤውን በዋናነት ያስተባበሩት አንደኛዋ የምክር ቤቱ አባል ጁሊያ ናቸው።
ከቢሮቸው ማብራሪያ ለማግኘት እንዲሁም የኢትዮጵያን መንግሥት ምላሽ ለማካተት ሞክረናል።
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5