አውሮፓ ኅብረት ለኢትዮጵያውያን የሹማን ሽልማትን አበረከተ

Your browser doesn’t support HTML5

አውሮፓ ኅብረት ለኢትዮጵያውያን የሹማን ሽልማትን አበረከተ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ እና የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማእከል ዋና ዳይሬክተር ያሬድ ኃይለማርያምን ጨምሮ ስምንት የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ግለሰቦችና ተቋማት የአውሮፓ ኅብረት ሹማን ሽልማት ተበረከተላቸው።

አውሮፓ ኅብረት ለሰብአዊ መብቶች መከበር፣ ለዴሞክራሲ፣ ለመቻቻል እና መሰል ሰብዓዊ ጉዳዮች የሚያበረክተውን የሹማን ሽልማት በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ ግንቦት 22 ቀን 2016 ዓ.ም ሸልሟል።

በኢትዮጵያ ሲሰጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የሆነው ይህ ሽልማት “ለሰብአዊ መብቶች፣ ለዴሞክራሲ፣ የሕግ የበላይነት፣ ለመቻቻልን እና እኩልነት የላቀ አስተዋጽዖ ላበረከቱ ሰዎች” የሚሰጥ ነው።

በሽልማት ሥነሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ፣ ኅብረቱ ለሰብአዊ መብት ጉዳዮች ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱን እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር ዳንኤል በቀለ፣ ሽልማቱ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በቀጠሉበት ወቅት መበርከቱ ትርጉም እንዳለው ገልፀው፣ የሽግግር ፍትሕ እና አገራዊ ምክክር የኢትዮጵያን ችግሮች ለመፍታት ብቸኛ አማራጮች ናቸው ብለዋል፡፡የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማእከል ዋና ዳይሬክተር ያሬድ ኃይለማርያምም አስተያየታቸውን ሰጥተውናል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።