የአውሮፓ ሕብረት $124 ሚልዮን ዶላር የሚሆን የሰብዓዊና የልማት ዕርዳታ ለሱዳን እንደሚሰጥ አስታውቋል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
የአውሮፓ ሕብረት $124 ሚልዮን ዶላር የሚሆን የሰብዓዊና የልማት ዕርዳታ ለሱዳን እንደሚሰጥ አስታውቋል።
ገንዘቡ ለአስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ፣ ለውሃ አቅርቦት፣ ለንፁህና ለጤና ጥበቃ፣ እንዲሁም ለትምህርት እንደሚውል የአውሮፓ ሕብረት ባለው ሰኞ ገልጿል። ከአካባቢያቸው የተፈናቀሉትንና የሚያስተናግድዋቸው ማኅበረሠቦችንም ለመርዳት ይውላል ብሏል።
የአውሮፓ ሕብረት የሰብአዊ ዕርዳታና የቀውስ አያያዝ ኮሚሽነር ክሪስቶስ ስታይሊንደስ ደቡብ ዳርፉርን በጎበኙበት ወቅት ከመኖርያቸው የተፈናቀሉትንና ከጎረቤት ደቡብ ሱዳን የተሰደዱትን መርዳት እንደሚስፈልግ አስገንዝበዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደሚለው ሱዳን ውስጥ 4.8 ሚልዮን የሚሆኑ ሰዎች ሰብአዊ ረድዔት ያስፈልጋቸዋል። አብዛኞቹ ያሉትም ዳርፉር መሆኑን ገልጿል።