ደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሰሞኑን በተከሰተው መጤ-ጠል ጥቃት ብዙ ጉዳት እንደደረሰባቸው እየተናገሩ ናቸው። የኢትዮጵያ መንግሥት እየተፈፀሙ ያሉ ሁከቶችን በብርቱ ቃላት አውግዞ የደቡብ አፍሪካ ባለሥልጣናት አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርጉ አሳስቧል።
አዲስ አበባ፣ ናይሮቢ —
ደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሰሞኑን በተከሰተው መጤ-ጠል ጥቃት ብዙ ጉዳት እንደደረሰባቸው እየተናገሩ ናቸው።
ብዙዎቹ የአካባቢው ነዋሪዎች ሱቆቻቸው እንደተሰበሩና ንብረቶቻቸው እንደተዘረፉ ገልፀዋል።
በደቡብ አፍሪካ የማኅበረሰብ ተወካይ የፀጥታው ሁኔታ አሁንም አለመሻሻሉን ለቪኦኤ ተናግረዋል።
ከዕሁድ ጀምሮ በደቡብ አፍሪካ በተለይ በጆሃንስበርግ ከተማ አቅራቢያ በሚገኙ ትናንሽ ከተሞችና መንደሮች ውስጥ በውጭ ሰዎች ላይ በተፈፀሙ መጤ-ጠል ጥቃቶች በርካታ ኢትዮጵያዊያን ንብረታቸውን መዘረፋቸውን ተናግረዋል።
የጥቃቱ ስፋትና ሁኔታ አስፈሪ መሆኑን ኢትዮጵያዊኑ ገልፀዋል።
በሌላ በኩል ኢትዮጵያዊያን የጥቃቶቹ ዒላማ መሆናቸውን ያስታወቀው የኢትዮጵያ መንግሥት እየተፈፀሙ ያሉ ሁከቶችን በብርቱ ቃላት አውግዞ የደቡብ አፍሪካ ባለሥልጣናት አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርጉ አሳስቧል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው ለአሜሪካ ድምፅ በስልክ በሰጡት ማብራሪያ “ጆሃንስበርግ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለዜጎች መረጃ እያደረሰና አስፈላጊውን ክትትልም እያደረገ ነው” ብለዋል።
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5