አዲስ አበባ —
በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎቹ ወደሀገራቸው እየተመለሱ መሆኑን የገለፀው የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናቱም ከሳዑዲ አቻዎቻቸው ጋር እየተነጋገሩ መሆናቸውን አስታውቋል።
በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ አምባሣደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ የተመራ የልዑካን ቡድን ወደ ሪያድ መጓዙ ተገልጿል፡፡
ሰሞኑን መግለጫ እያወጡ ያሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ግን መንግሥት ለእርምጃው ዘግይቷል፥ የበለጠ ሥራም ይጠብቀዋል ይላሉ።
በጉዳዩ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ለነገ ጥሪ የበተነው መኢአድ የሌሎች አንዳንድ ሃገሮች ዜጎች መብቶች ከኢትዮጵያዊያኑ በተሻለ ሁኔታ እንደሚጠበቅና በኢትዮጵያዊያን ላይ ግፍ ሲደርስ ግን የአሁኑ የመጀመሪያ አለመሆኑን የድርጅቱ ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መሃሪ አመልክተዋል፡፡
ዛሬ መግለጫ ያወጣው ሰማያዊ ፓርቲ ደግሞ ነገ ዐርብ፣ ኅዳር 6 / 2006 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው የሣዑዲ አረቢያ ኤምባሲ አቅራቢያ ሰልፍ ጠርቷል፡፡
የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነት የአዲስ አበባ አስተዳደር ሕጋዊ ዕውቅና ባይሰጣቸውም ሰልፉ ሕጋዊ ነው ብለዋል፡፡
በደንቡ መሠረት በኤምባሲዎችና በዓለምአቀፍ ተቋማት መሥሪያ ቤቶች በመቶ ሜትር ርቀት ውስጥ መሰብሰብ የማይቻል ሲሆን ይህንን አክብረው ሰልፋቸውን እንደሚያካሂዱ ገልፀዋል፡፡
“እኛ የምንፈልገው ኤምባሲ ውስጥ መግባት ሳይሆን ተቃውሟችንን ማሰማት ነው” ብለዋል - አቶ ይልቃል ለቪኦኤ በሰጡት ቃል፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5