አሥር የተለያዩ ኢትዮጵያዊያን ድርጅቶች ዋሺንግተን ዲሲ ላይ ከትናንት በስተያ ዓርብ፣ ጥር 5 እና ቅዳሜ ጥር 6 ጉባዔ አካሂደዋል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ጉባዔው የተዘጋጀው የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ምክር ቤትና የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ በሚባሉ ሦስት ድርጅቶች መሆኑን አስተባባሪዎቹ ለቪኦኤ ገልፀዋል።
በጉባዔው ላይ የተገኙት ከአስተባባሪዎቹ ድርጅቶች በተጨማሪ ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኅብረት - ኅብረ-ሕዝብ፣ ዳግማዊ አርበኞች ንቅናቄ፣ ቱሣ የኢትዮጵያ ትንሣዔ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት እና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሠላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ኅብረት እንዲሁም በጉባዔው መዝጊያ ዕለት የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር መሆናቸው ታውቋል።
የጉባዔው ተሣታፊዎች “የቀውጢ ጊዜ አገር አድን” በሚል የተሠየመ ኮሚቴና ክፍተቶችን ለመሙላትና የጋራ መድረክ ለመፍጠር የሚሠራ ሌላ ኮሚቴ ማቋቋማቸውን አስተባባሪዎቹ ተናግረዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5