ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን መብቶች መከበር የሚሟገተው ዓለምአቀፍ ጥምረት የ30 ሺህ ዶላር ድጋፍ ለዓለምአቀፉ የፍልሰት ድርጅት - አይኦኤም ዛሬ አበረከተ፡፡
ዋሺንግተን ዲ.ሲ. —
ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን መብቶች መከበር የሚሟገተው ዓለምአቀፍ ጥምረት የ30 ሺህ ዶላር ድጋፍ ለዓለምአቀፉ የፍልሰት ድርጅት - አይኦኤም ዛሬ አበረከተ፡፡
ሥጦታውን ዋሽንግተን ዲ.ሲ በሚገኘው የአይኦም ፅ/ቤት ተገኝተው ያበረከቱት የጥምረቱ ሊቀመንበር አርቲስት ታማኝ በየነ፣ የጥምረቱ የዲፕሎማሲና የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ዶክተር አክሎግ ቢራራ፣ የጥምረቱ የበላይ አማካሪ አቶ ንአምን ዘለቀ፤ የገንዘብ መምሪያ ኃላፊዋ ወ/ሮ ሂሩት ልሣነወርቅ ናቸው፡፡
ሥጦታውን የተረከቡት የአይአኤም የዋሽንግተን ዲ.ሲ. ቢሮ የውጭ ግንኙነቶች ኃላፊ ማሪያ ማሪኖ ካለፈው መጋቢት ጀምሮ ቀውሱን በማስወገድ ላይ እየሠራ ያለ ድርጅታቸው እስከአሁን 140 ሺህ ኢትዮጵያዊያንን ከሳዑዲ አረቢያ ማውጣቱን አመልክተው በአሁኑ ጊዜ የቅድሚያ ትኩረት እየሰጡ ያሉት ለሴቶችና ለሕፃናት መሆኑን አስረድተዋል፡፡
አይኦኤም ለድጋፍ ከጠየቀው የ15 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ እስካሁን ያገኘው 2.5 ሚሊዮን ዶላር ብቻ መሆኑን ሞሪኖ ጠቁመው የአሁኑን የኢትዮጵያዊያኑን ዓይነት ድጋፍ ድርጅታቸው እንደሚያደንቅና ማንኛውምንም እርዳታ እንደሚቀበል ከተረጂዎች ጋርም እየሠራ ያለው በቀጥታ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ለተጨማሪ ዝርዝር የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5