“ሰዎች በሚሉት ጋር ላትስማማ ትችላለህ፤ ማለት የሚፈልጉትን ነገር የማለት መብታቸውን ግን ልታከብር ይገባል” በኢትዮጵያ የአሜካ ኤምባሲ ቃል አቀባይ ኒኮላስ ባርኔት ናቸው ይህንን ያሉት።
ዋሽንግተን ዲሲ —
ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ እጅግ መሠረታዊ ከሆኑ የሰው ልጅ መብቶች አንዱ መሆኑን ያስታወሰው በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ሰዎች መብቶቻቸው እንዳልተከበሩ ሲሰማቸው ጥያቄ ማንሳት የሚችሉት በዚሁ መብት እንደሆነም ጠቁሟል።
የኤምባሲውን የማኅበራዊ ሚዲያ ዌብሳይት የሚከታተሉ ሰዎች ገንቢና አክባሪ በሆነ መንገድ እንዲሳተፉ ቃል አቀባዩ ባርኔት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5