ኬንያ የተሰደዱ ኢትዮጵያውያን ተፈናቃዮች የምግብና መጠለያ ችግር ገጠማቸው

ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ ተሰደው የሚገኙ ተፈናቃዮች ምግብና መጠለያ በማጣት ችግር ላይ መሆናቸውን ተናገሩ። ለተፈናቃዮቹ ዕርዳታ እያደረገ ያለው የኬንያ ቀይ መስቀል በበኩሉ ማምሻውን ባወጣዉ መግለጫ ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ በመሰደድ ላይ ያሉ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ መሆኑን ገልፀዋል።

ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ ተሰደው የሚገኙ ተፈናቃዮች ምግብና መጠለያ በማጣት ችግር ላይ መሆናቸውን ተናገሩ። ለተፈናቃዮቹ ዕርዳታ እያደረገ ያለው የኬንያ ቀይ መስቀል በበኩሉ ማምሻውን ባወጣዉ መግለጫ ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ በመሰደድ ላይ ያሉ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ መሆኑን ገልፀዋል።

የስደተኞቹን ሁኔታ በማሰስ ላይ ያለው የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ /ዩኤንኤችሲአር/ ብዙዎች ባዶ እጃቸዉን ከቤታቸው ስለተባረሩ አስቸኳይ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ሲል አሳስቧል።

በሺሕዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ዜጎች መጋቢት 1/ 2010 ዓ.ም በሞያሌ የደረሰውን ግድያ ሸሽተዉ ኬንያ ግዛት በ4 ግዜያዊ መጠለያ ሰፍረው ይገኛሉ። የኬንያ መንግሥት ከዕርዳታ ድርጅቶች ጋር ለተፈናቃዮቹ የምግብ እንዲሁም የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ ላይ ቢሆንም የቀረበው ዕርዳታ በቂ ባለመሆኑ ተገቢ ዕርዳት ማድረግ አለመቻሉን ገልጿል።

ሙሉውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ።

Your browser doesn’t support HTML5

ኬንያ የተሰደዱ ኢትዮጵያውያን ተፈናቃዮች የምግብና መጠለያ ችግር ገጠማቸው