ከምስራቅ ሀረርጌ የተለያዩ ቦታዎች ተይዘው ታስረው የነበሩ አንድ የ45 ዓመት አዛውንት እና አንድ የዩኒቨርስቱ ተማሪ ስለ "ጦላይ የእስረኞች ማቆያ ማዕከል" ቆይታቸው አጫውተውናል። በዚህ ዘገባም የመጀመሪያ ቆይታቸው ምን እንደሚመስል የተናገሩትን ይዘናል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ከታወጀ በኋላ የታሰሩ ከ11 ሺህ በላይ እስረኞች በተለያዩ ቦታዎች በሁለተኛ ዙር "የተሃድሶ ስልጠና" ወስደው መለቀቃቸው ተገልጿል። ከእነዚህ ውስጥ የበዛውን ቁጥር የሚይዙት በጦላይ የማቆያ ማእከል ስልጠና የወሰዱት እንደሆኑም የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ኮማንድ ሴክረትሪያት በጥር ወር መጨረሻ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ማስታወቁ ይታወሳል።
ጽዮን ግርማ ከጦላይ ማቆያ ማዕከል የተለቀቁ ሁለት እስረኞችን አነጋግራ። ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች።
Your browser doesn’t support HTML5