አቶ ልደቱ በሌላ አየር መንገድ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ መዘጋታቸውን ገለጹ

አቶ ልደቱ አያሌው

አቶ ልደቱ አያሌው

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ረዥም ዓመታትን ባስቆጠረ ተሳትፏቸው የሚታወቁት አቶ ልደቱ አያሌው፣ በአሜሪካን ሀገር ሲከታተሉ የነበረውን ሕክምና ጨርሰው ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ለጉዞ የመረጡት የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዳይሳፈሩ እንደከለከላቸው እና በሌላ አየር መንገድ ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ ተናግረዋል።

Your browser doesn’t support HTML5

አቶ ልደቱ በሌላ አየር መንገድ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ መዘጋታቸውን ገለጹ

የኢትዮጵያ የአየር መንገድ አትላንታ ቢሮ ኃላፊዎች፣ ከዋናው ቢሮ እርሳቸውን ለማስተናገድ እንዳይችሉ የክልከላ ትዕዛዝ እንደተሰጣቸውና ክልከላውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ማስነሳት ከቻሉ ብቻ እንደሚያስተናግዷቸው እንደገለጹላቸው ተናግረዋል፡፡

አቶ ልደቱ ቀኑን ሳይጠቅሱ በሌሎች አየር መንገዶች ትኬት በመቁረጥ በቅርቡ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ማሰባቸውንም ለአሜሪካ ድምጽ ጨምረው አስታውቀዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድን፣ በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ ኢምባሲንና የኢትዮጵያ ኢምግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ኃላፊዎችን ምላሽ ለማካተት የአሜሪካ ድምጽ ከትላንት ጀምሮ ያደረገው ጥረት አልተሳካም።